Zellan Patterns Left
Zellan Patterns Right

በእንዳሻዉ ፈይሳ

Covid-19 የጥበቡ ዓለም ፈተና

Covid-19 ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የዓለም ኢኮኖሚ ሲዋዥቅ ቆይቷል:: ጊዜዉ ደርሶ በሽታዉ ወደ ኢትዮጲያ ሲገባ ድሮዉንም በቋፍ የነበረዉ የአገሪቷ ኢኮኖሚ ቁልቁል መዉረዱን ለመጠቆም የአገሪቷ ዋነኛ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነዉ የኢትዮጲያ አየር መንድ አጣዉ ያለዉን የገቢ መጠን መጥቀስ በቂ ማስረጃ ይሆናል::

ከመንግስትም ሆነ ከግል ተቋማት ይሄነዉ የሚባል ድጋፍ የማይደረግለት የጥበቡ ዘርፍ በዚ በሽታ ከተጎዱ የስራ መደቦች አንዱ ነዉ:: በኢትዮጲያ ከCovid-19 በፊት የሚካሄዱ አብዛኞቹ ጥበብ ተኮር ስራዎች በቀጥታ ከመድረክ ለተመልካች የሚቀርቡ ነበሩ:: ከአንጋፋዎቹ እስከ ጀማሪ የጥበብ ሰዎች ይሄን መንገድ በብቸኝነት ሲጠቀሙበት ቆይተዋል::

ነገርግ Covi-19 ወደ ኢትዮጲያ ከገባ በጟላ የጥበብ ዝግጅቶችን በቀጥታ ሰዉ በተሰበሰበበት ቦታ ማቅረብ ከበሽታዉ የመተላለፍ አቅምና አደገኛነት አንፃር የማይታሰብ ነዉ:: ለዚያም ነዉ ከአንጋፋዎቹ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ትያትር እና አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሲስን ከመሳሰሉ ትላልቅ የጥበብ ማዕከላት ጀምሮ ሲኒማ ቤቶች፣ የምሽት መዝናኛዎች፣ ቲያትር ቤቶችን ጨምሮ እስከ ትንንሽ የግጥምና የጀማሪ አርቲስቶችን ስራ እስከ ሚያቀርቡ ስፍራዎች፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ የጥበብ ቦታዎች በራቸዉን በፍጥነት ለመዝጋት የተገደዱት::

በዚህም ምክንያት በጥበቡ ዓለም ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል:: የጥበብ ስራዎችን በቀጥታ ከማቅረብ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ያለዉ ዝግጁነት አናሳ ከመሆኑም በዘለለ በአገሪቷ ዉስጥ ያለዉ የመረጃ መረብ ፍጥነት ዝቅተኛ መሆን፣ ክፍያለዉ ለአብዛኞቹ ጀማሪ የጥበብ ሰዎች በአንፃራዊነት ዉድ መሆን፣ ሰፊዉ ማህበረሰብ የመረጃ መረብን ጠቀሜታን አለመረዳትና የመሳሰሉት ችግሮች ተደራርበዉ ከ Covid-19 በጟላ ለጥበቡ ዓለም ሰዎች ነገሮችን አስቸጋሪ አድርገዋቸዋል::

በዚ ሁሉ ዉጣ ዉረድ ዉስጥ አንዳንዶች ራሳቸዉን ከጊዜዉ ጋር አዘምነዉ በመረጃ መረብ በኩል ስራዎቻቸዉን ለማቅረብ ጥረት እያደረጉም ይገኛሉ:: "Ethiopian Records" የኢትዮጲያ ልጅ በ YouTube በኩል ብቅ ብሎ በሳምን ለተወሰኑ ቀናት በቀጥታ አድናቂዎቹን እያዝናና ይገኛል:: ዘላን የፈጠራና የባህል ማዕከልም ራሱን በተለያዩ መንገዶች እያስተዋወቀና ከጊዜዉ ጋር ለመሄድ ጥረት እያደረገ ነዉ:: በድህረገፁ ላይ በየጊዜዉ ማሻሻያዎችን በማድረግና የስዕል ማሳያ ጋለሪዉን በቤታቸዉና በስራ ቦታቸዉ ላሉ መምጣት ሳይጠበቅባቸዉ ባሉበት ቦታሆነዉ ይጎበኙ ዘንድ 360 ድግሪ ቪድዮ ይዞ ቀርቧል:: ዘላን በድረገፁ በየሳምንቱ ከሚያወጣቸዉ ፅሁፎች በተጨማሪም "The journal of a non-reader " የተባለዉን የአሌክሳንደር ህዝቂያስ መፅሀፍንም በድረገፁ ላይ በመጫን በቀላሉ ለመድረስ ጥረቱን ቀጥሏል::

ችግርና አስከፊ ወቅቶች ጥበብና ጥበበኞች የሚፈኩበት በመሆኑ እኛም በእንደዚ አይነት ሰዓት ከጥበብና ከጥበብ ፈጣሪዎች ጎን በመቆም አጋርነታችንን ማሳየት አለብን::